ስለ Huawei Health እና ግላዊነት መግለጫ
መጨረሻ የዘመነው፦ ኦክቶበር 1፣ 2019
Huawei Health ከባለሙያዊ የአካል ብቃት ስልጠና እና የጤና አገልግሎቶች በተጨማሪም የተለያዩ የጤንነት እና የአካል ብቃት መከታተያ ባህሪያትን ያቀርብልዎታል። ይህ መተግበሪያ ስራ ላይ በሚውልበት ጊዜ ከበይነመረብ ጋር መገናኘት አለበት፣ እና የሚከተሉት የፈቃዶች ወይም የባህሪያት መዳረሻ ያስፈልገዋል፦ አካባቢ፣ ብሉቱዝ፣ ካሜራ፣ ማይክሮፎን፣ እውቂያዎች፣ የጥሪ መዝገቦች፣ ስልክ እና ማከማቻ። እንዲሁም የሚከተሉትን መረጃዎች መሰብሰብና ማሰናዳት አለበት፦
• የእርስዎ የመሳሪያ ለዪ፣ የመሳሪያ ቅንብሮች፣ የግል ቅንብሮች፣ የIP አድራሻ እና የአውታረ መረብ አይነት ጨምሮ የመሳሪያ እና የአውታረ መረብ መረጃ።
• የእርስዎ የHUAWEI መታወቂያ እና ይህ መተግበሪያ ይበልጥ ትክክለኛ የሆነ ውሂብ እንዲያገኝ የሚያግዙ የእርስዎ ቁመትና ክብደት ጨምሮ የግል መረጃ።
• የመሳሪያ አካባቢ፣ የሰውነት እንቅስቃሴ አቅጣጫ፣ አይነት፣ የቆይታ ጊዜ፣ የሩጫ ቅርጽ፣ የእርምጃ ብዛት፣ ርቀት፣ ካሎሪዎች፣ የተገኘው ከፍታ፣ ከፍተኛው የኦክሲጅን ፍጆታ እና የሰውነት እንቅስቃሴ ልብ ምትን ጨምሮ የአካል ብቃት ውሂብ። ይህ ውሂብ ለማከማቻ እና ለማሳያ ዓላማ ይሰበሰባል።
• የሚከማችና የሚታይ እንቅልፍ፣ የልብ ምት፣ ጭንቀት እና የሰውነት ስብ መቶኛ ጨምሮ የጤንነት ውሂብ።
የእርስዎ የጤና እና የአካል ብቃት ውሂብ ሚስጥራዊነት ያለው የግል መረጃ አለው። ይህ ውሂብ ስራ ላይ የሚውልበት መንገድ – ወደ Huawei Health Cloud ይሰቀል እንደሆነ፣ ወዴት እንደሚሰቀል እና በማን እንደሚቀናበር ጨምሮ – በእርስዎ አካባቢ፣ በመረጡት አገር/ክልል ወይም ባቀረቡት የመለያ መግቢያ መረጃ የሚወሰን ነው። ተጨማሪ ዝርዝሮችን ለማግኘት ወደ እኔ > ቅንብሮች > የግላዊነት ቅንብሮች ይሂዱ።
ይህ መተግበሪያ የሚሰራው ከላይ የተገለጸው መረጃ እንዲሰበሰብ ከተስማሙና የሚያስፈልጉትን ፈቃዶች ከሰጡ ብቻ ነው። ከላይ ያለው የመረጃ መሰብሰብና መሰናዳት ለማቆም እና እርስዎ የሰጧቸውን ፈቃዶች ለመሻር መተግበሪያውን ያራግፉት ወይም ወደ እኔ > ቅንብሮች > የግላዊነት ቅንብሮች ይሂዱና ለማይፈልጉት መረጃ ያሉትን መቀየሪያዎች ያጥፉ።